በሺዎች የሚቆጠሩ የአማርኛ ምሳሌዎችን ያስሱ።
ከ3,328 ምሳሌዎች 1861–1880 እያሳየ
ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ የለም
telegramሀምሌ ቢያባራ በጋ ይመስላል
telegramየፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ቀማሽ
telegramነገር ያለዳኛ ትብትብ ያለመጫኛ
telegramድመት ውስጥ ውስጡን አውሬ ናት
telegramለሰው ሞት አነሰው ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ
telegramበጠራ ተሻገር በተሳለ ምተር
telegramወዳጅ ይመጣል ከራያ ጠላት ይወጣል ከጉያ
telegramየፈሪ ገዳይነት ለማታ
telegramያብዬን እከክ ወደ እምዬ ላከከ
telegramሁለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
telegramቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብለህ አሳልፈው
telegramየሚውል ሆድ ማለዳ ያረግዳል
telegramቄስ እበር አረመኔ ከማህበር
telegramያኖሩት እንቅርት መለያ ይሆናል
telegramበሬ ሆይ በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ እልም ካለው ገደል ወደቅክብን ወይ
telegramጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ
telegramሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ
telegramበእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
telegramተንኮለኛ ገደል ዝንጀሮ ይጥላል በሬ ያሳልፋል
telegram