በሺዎች የሚቆጠሩ የአማርኛ ምሳሌዎችን ያስሱ።
ከ3,328 ምሳሌዎች 2021–2040 እያሳየ
ተሻገር ከወንዙ ጉድ እንዳያበዙ
telegramያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እትህ
telegramላሊበላ የቃሉን አይበላ
telegramዘመን የሚወልደውን ንጉስ የሚፈርደውን የሚያውቅ የለም
telegramድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በከብቱ
telegramሀስት እያደር ይቀላል እውነት እያደር ይበራል
telegramተባቄላ አይጠፋም ዲቃላ ከጠላ አይታጣም አተላ
telegramለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው
telegramእንጣጥ እንደ ፌቆ ሙልጭ እንደ ስብቆ
telegramሸክላ ቢጥሉት ገለባ
telegramየለመደ ፈረሰኛ ዛብ አይጨብጥ እርካብ አይረግጥ
telegramእንደ ልብ የለም ነዳጅ እንደ ልብ የለም በራጅ
telegramተመልከት አላማህን ተከተል አለቃህን
telegramያለው ይበላል የሌለው ያፈጣል
telegramእንዳያማ ጥራው እንዳይበላ ግፋው
telegramያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ
telegramያልወለደኩት ልጅ አባ አባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
telegramእኔ በልጄ ሳዝን ልጄ በልጁ ያዝን
telegramበባዶ ቢቆጡ በጨለማ ቢያፈጡ
telegramሀጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል
telegram