Proverbs

Explore thousands of Amharic proverbs.

Showing 1201–1220 of 3,328 proverbs

1201

ጸሀይ ካልወጣ ከሰፈረበት አይነሳ አንበጣ ሴት ምክንያት አታጣ

telegram
1202

የባል ደግነቱ ውሽሜን መርሳቱ

telegram
1203

ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመካከር

telegram
1204

ለወሬ የቸኮለ እናቱን በመንገድ ይረዳል

telegram
1205

ትገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ

telegram
1206

እኛ ምን አገባን በሰው ፖለቲካ እኛንም አይንኩን እኛም ሰው አንነካ

telegram
1207

ትምህርትም እንደ ኮት ፋሽኑ አለፈበት

telegram
1208

ፍጥም ያቆማል እርቅ ይጠቀልላል

telegram
1209

ዘምቶ ያረጀ በልቶ ያፈጀ

telegram
1210

ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል

telegram
1211

ጅብ እንኳን ጓደኛውን ይጣራል

telegram
1212

እውር ሲቀናጣ ምርኩዙን ወርውሮ ፍለጋ ይገባል

telegram
1213

እናቲቱን አይተህ ልጅቷን አግባ

telegram
1214

ቅማል በጥፍር ቢድጧት ራስ ደህና አለች

telegram
1215

ራስ ተላጭቶ ወለባ ልባልባ ታጥቆ አዛባ

telegram
1216

ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል

telegram
1217

ዳኛ ሳለ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር

telegram
1218

ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው

telegram
1219

የአሳ ግማቱ ከወደ ጭንቅላቱ

telegram
1220

የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይመታል

telegram