Explore thousands of Amharic proverbs.
Showing 2041–2060 of 3,328 proverbs
እግዜር እባብን ልቡን አይቶ እግር ነሳው
telegramነገሬ በከንፈሬ
telegramእንደ መረብ ሸፍኖ እንደ እንቁላል ደፍኖ
telegramሌባን ሌባ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው
telegramተመሮጥ ማንጋጠጥ ይሻላል
telegramተሁሉም ያው ወንድም ቢከፋም ቢበጅም
telegramነገር ወዳጅ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
telegramይሉኝ አይል ጸሀፊ ከሙሴ ይገድፋል
telegramየልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢሰዱህ
telegramሊጣላ የመጣ ሰብብ አያጣም
telegramፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛን ምን አቆመው
telegramድመትና አይጥ እሳትና ጭድ
telegramእንዲህ ሊታረፈን ለሚስቴ ነፈግኋት
telegramእንደ አጥር እንደ ቅጥር
telegramተከናንቦ የሚበላውን ተጎንብሰህ ግባበት
telegramዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ
telegramተቀምጠው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ያስቸግራል
telegramለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ
telegramለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር
telegramውሀ ቢወቅጡት መልሶ እንቦጭ ነው
telegram