Explore thousands of Amharic proverbs.
Showing 2961–2980 of 3,328 proverbs
ንጉስ አንጋሹን ቤተክርስቲያን ቀዳሹን
telegramይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጉልበቱ
telegramይበጃል ያሉት መድሀኒት አይን አጠፋ
telegramያላዞረ ሲዞር አደረ
telegramያባት ወርቅ ባለዝና እህል ለቀጠና
telegramየማያዋጣ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
telegramሸማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን
telegramእውነትና ንጋት እያደር ይታያል
telegramተድረው ቢመለሱ የውሀ መንገድ ረሱ
telegramለወሬ የለው ፍሬ ለአበባ የለው ገለባ
telegramትተውት የማይሄዱትን ባልንጀራ አይቀድሙትም
telegramያበደና የወደደ አንድ ነው
telegramተግደርዳሪ በልቶ ሽሮ ተበዳሪ
telegramነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው
telegramየግመል ሽንት ይመስል ሁሌ ወደኋላ
telegramፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት
telegramዘመዱን ያማ እራሱ ገማ
telegramካለቀ መቆጠብ ከመሽ መንጠብጠብ
telegramደንቆሮ የሰማ ለት ያብዳል
telegramሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ
telegram