Proverbs

Explore thousands of Amharic proverbs.

Showing 1881–1900 of 3,328 proverbs

1881

ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል

telegram
1882

እጅ እሾህን ይነቅሰዋል ጥጋብ ሞትን ያስረሳዋል

telegram
1883

ያምላክን ነገር ስንቱን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው

telegram
1884

ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል

telegram
1885

ቀንዳምን በሬ ቀንድ ቀንዱን

telegram
1886

የሞተው ባልሽ የገደለው ውሽማሽ

telegram
1887

ያባቱን ቢሰጡት ህይወቱ ያባቱን ቢነሱት ሞቱ

telegram
1888

ሰው ከሞተ የለ ንስሀ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሀ

telegram
1889

ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም

telegram
1890

ዶሮ ከጮኸ ሌሊት ከደብረ ታቦር ወዲያ ክረምት የለም

telegram
1891

ዞሮ ዞሮ የዶሮ አንገት በማሰሮ

telegram
1892

ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አባት አይወቀስ

telegram
1893

ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል

telegram
1894

እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ደንዳና ይሞታል

telegram
1895

የሴት ልባም ያህያ ቀንዳም

telegram
1896

ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት

telegram
1897

ያገባሽ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ

telegram
1898

ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ

telegram
1899

ሀኪም የያዘው ነፍስ ባያድር ይውላል

telegram
1900

ውሀ የጥቅምት ነበርሽ ታዲያ ማን ይጠጣሽ

telegram